በታደሰ በላይ (ሠቆጣ ፤ ታኅሳስ 07፥ 2016 ዓ.ም)
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከተለያዩ በጎ አድራጊዎች የተገኘ ከ10 ሚሊዮ ብር በላይ ግምት ያላቸው የእለት ደራሽ ምግብ እና አልሚ ምግብ ድጋፍ ተደርጓል። የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ተወካይ ዲ/ን ግርማ ታከለ ይህ በዋግ ልማት ማኅበር አስተባባሪነት ከሀገር ውስጥ እና ውጭ ከሚገኙ በጎ አድራጊ ወገኖች የተገኘ ድጋፍ ሲሆን አማራ ባንክ (1176 ኩንታል)፣ ላይፍ ሴንተር (59 ኩንታል)፣ መቄዶንያ (500 ኩንታል)፣ ንቡረ ዕድ ቆሞስ አባ ብርሃነ ሥላሴ ብርሃኑ (68 ኩንታል)፣ አቶ ንጉሴ ጭቋላ (50 ኩንታል)፣ አሜሪካን ሀገር የሚኖሩ የዋግ ተወላጆች (82 ኩንታል) አልሚ ምግቦች በሠሀላ፣ ዝቋላና አበርገሌ ወረዳዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ድጋፍ አድርገውልናል ሲሉ ገልፀዋል።
ዲ/ን ግርማ ታከለ አከለውም ይህንን ድጋፍ እስከ ሰቆጣ ድረስ ለማድረስ 5 ተሣቢ የተሽከርካሪዎች ጥቁር አባይ ትራንስፖርት ድጋፍ ያደረገልን ሲሆን የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) ሠብአዊ ድጋፍ አሠባሣቢ ኮሚቴ የደርሶ መልስ ነዳጁን በመሸፈን ድጋፎችን ሠብስቦ ሰቆጣ እንዲደረስ አድርጓል ብለዋል። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አደጋና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ በበጀት ዓመቱ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ሙሉ በሙሉ ዝቋላ እና አብርገሌ ወረዳ በከፊል ድርቅ የተከስተ ሲሆን ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ወገኖቻችን ድጋፉን መላካቸው አመስግነው በቀጣይ ጊዜያት ድጋፉ አጓጉዘው ድጋፍ ለሚገባቸው የህብረተስብ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን እናደርጋለን ሲሉ ገልፀዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ በአስተዳዳሪ ማዕረግ መንገድ መምሪይ ኃላፊ አቶ ፀጋው አሸቴ እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር በአሁኑ ወቅት ከ180 ሽህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ በመሆኑም የቅን ልቦችን ድጋፍ የሚሹ ህፃናት፣ እናቶችና አረጋዊያንን ለመደገፍ የዋግ ተወላጆች እና ወዳጆች ፣የሀይማኖቶት ተቋማት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሙሉ ይህንን መሰል ድጋፎችን እንዲያደርጉም መልዕክት አስተላልፈዋል። ድጋፋን ያስረከቡት የአማራ ባንክ የሰቆጣ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ እሸቱ ሽፈራው ባንኩ ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመዋጣት ድጋፍ አድርገናል ነው ያሉት። ድጋፉ ከሠራተኞቹ እና ከባንኩ ቦርድ በተገኘ የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተገዛ 1 ሺህ 176 ኩንታል ፊኖ ዱቄት ነው፡፡ ባንኩ ድጋፋን አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ሥራ አስኪያጁ ሌሎች ድርጅቶችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የተገኙት የሰቆጣ ከተማ የሃይማኖት አባት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አሥኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ኃይሌ አለሙ የሃይማኖት ተቋማትም ማኅበራዊ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።