`

[ታደሠ በላይ፤ ሠቆጣ፣ የካቲት 11፥2016 ዓ.ም]


በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል ከ3,000,000 (ሶስት ሚሊዬን) ብር በላይ የሚገመት 703 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ ተደረገ። የሌተናል ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ቤተሰቦች እና ዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ በዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) አስተባባሪነት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለድርቅ ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖች የሚውል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት 7መቶ 3 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ አድርገዋል። ድጋፉን ያስረከቡት ዋልማ ዋና ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር ኃይሌ ወልዴ አዲስ አበባ በተቋቋመው ዓብይ ኮሚቴ አማካኝነት በብሔረሰብ አስተዳደራችን የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም የሚያስችል እስካሁን ከ153 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ መደረጉን ገልፀው በዛሬው ዕለትም ከሌተናል ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ቤተሰቦች እና ከዓባይ ኢንሹራንስ አ.ማ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት 703 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ድጋፍ መደረጉን የተናግረዋል። የዋልማ አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የፋይናንስና ሎጅስቲክ ንዑስ ኮሚቴ አባልና ፀሀፊ ዲ/ን ግርማ ታከለ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተከሰተውን ድርቅ ለመሻገር በሚደረገው ርብርብ እስካሁን በተለያዩ በጎ አድራጊዮች ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፣ በዛሬው ዕለትም ከዓባይ ኢንሹራንስ ማኅበር 574 እና ከሌተናል ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ቤተሰቦች 129 ኩንታል በጠቅላላ 703 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት ማስረከባቸውን ገልፀዋል። አክለውም በቀጣይ ከስብዓዊ ድጋፍ ባሻገር ለእንሰሳት መኖ ለማቅረብ ማኅበሩ እየሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ልማት ማኅበሩ ከማስተባበር በተጨማሪ ትራንስፖርት ወጭን ሸፍኖ ከዓባይ ኢንሹራንስ እና ከሌ/ጀኔራል ኃይሉ ከበደ ቤተሰቦች የተገኘ 703 ኩንታል ለዕለት ምግብ የሚሆን የበቆሎ ዱቄት መረከባቸውን ተናግረዋል። በባለፈው የክረምት ወቅት የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ እስካሁን ወደ 28 ሺ 5 መቶ ኩንታል የዕለት ምግብ ለ197 ሺ ተጋላጮች በአንድ ዙር ተደራሽ መደረጉንም አክለዋል። እስካሁን ሰብዓዊ ድጋፎች በሚፈለገው ልክ ባይሆንም ተሳትፎው የተሻለ ነው። ለእንሰሳት መኖ አቅርቦት ግን ፈታኝና አሳሳቢ ችግር መሆኑን በማስረዳት በየአካባቢው በርካታ እንሰሳት በመኖ እጥረትና ውሃ ጥም እየሞቱ ስለሆነ በአገር ውሰጥም በውጭም የምትኖሩ የዋግ ተወላጆች እና የዋግ ህዝብ ወዳጆች ፣የሀይማኖቶት ተቋማት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሙሉ ለዋግ ህዝብ አፋጣኝ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል አቶ ምህረት ።

ህብረት ለዋግ ልማት!

Categories : Categories : Partners & Supporters

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *