`

[ታኅሳስ 09 ፥ 2016 ዓ.ም]

ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን  በ2015/16 ዓ.ም የመኸር ዘመን የተከሠተው የዝናብ እጥረት በዞኑ ሶስት ወረዳዎች ውስጥ ለርሃብ የሚዳርግ ከባድ ድርቅ አስከትሏል፡፡ ድርቁ የከፋ ሰብአዊ ጉዳት እንዳያደርስ የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) ከተለያዩ ደጋፊ አካላት አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እያሰባሰበ ይገኛል። በታህሳስ ወር 2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት አዲስ አበባ የሚገኘው አስቸኳይ የሰብአዊ  እርዳታ አሰባሳቢ ግብረ- ሃይል (Task Force) ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና በጎ አድራጊ ግለሰቦች ያሰባሰበውን ድጋፍ በተመለከተ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች የተሰራውን ዘገባ እዚህእዚህእዚህ ያገኙታል። ዋልማ ድጋፍ ላደረጉልን የበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽንን፣ የወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነዝ ግሩፕን፣ የመቄዶንያ ተራድኦ ድርጅትን፣ የአማራ ባንክን እና ላይፍ ሴንተርን በተረጂዎች ስም ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።

የዋግ ልማት ማኅበርን በሃሳብዎ፣ በእውቀትዎ፣ በገንዘብዎ ይርዱ።

Categories : Categories : Partners & Supporters, WDA

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *