`

በ ዋግ ኽምራ ዞን በ2015/16 ዓ.ም የመኸር ዘመን የተከሠተው የዝናም እጥረት ባስከተለው ከባድ ድርቅ በ ሰሀላ ሰየምት ፥ ዝቋላ ፥ አበርገሌ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 26 ቀበሌዎች ለርሃብ የሚዳርግ ከባድ ድርቅ ተከስቷል፡፡ ለአብነት ያክል የሚከተሉትን ዘገባዎች ይመልከቱ BBC (23 November 2023), VOA (27 November 2023), AS (17 November 2023), DW (10 ኅዳር 2016 ዓ.ም), AMM (22 October 2023), BBC (03 October 2023), ኢዜአ ( 03 ታህሳስ 2016 ዓ.ም), BBC (03 October 2023), VOA (02 October 2023) ።

እነዚህን ወገኖቻችንን ከአስከፊ የርሃብ እልቂት ለመታደግ የእርሶዎንም ሰብአዊ ድጋፍ አጥብቀን እንሻለን እና ትብብርዎ አይለየን። የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ) ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር የአስቸኳይ ሰብአዊ ርዳታ እያሰባሰበ ይገኛል። ስለሚያደርጉት ሁለንተናዊ ድጋፍ በቅድሚያ እናመሰግናለን።

የዋግ ልማት ማኅበር (ዋልማ)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር
1000036134438

Categories : Categories : News

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *